Head's Photo

Message from the Head

ወ/ሮ ባንቹ ፀህይ የጉለሌ ክፈለ ከተማ ባህል እና ኪነ-ጥበብና ጽ/ቤት ኃላፊ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የባህል፤የታሪክና የቅርስ ሀብቶች ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመለወጥና ዘርፉን በተገቢው መንገድ ለማሳደግና ለመምራት የሚስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችን በመቅረፅ ወደ ስራ መግባቷ ይታወቃል፡፡እነዚህ ፖሊዎች ራሳቸውን የቻሉ አዋጆች ፤ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ አሰራሮች ተቀርጸውላቸው ወደ ተግባር በመገባቱ ባለፉት የለውጥ አመታት ህብረተሰቡ የራሱን ባህል፤ ወግ፤ ማንነት፤እሴት እና ቱፊት ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላላፍ እንዲችል ከፍተኛ እድል አግኝቷል፡፡ የጉለሌ ክፈለ ከተማ ባህል እና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ይህንኑ ተከትሎ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ በሀገር ደረጃ የተደነገጉና ተግባር ላይ የዋሉ ፖሊሲዎችን፤አዋጆችን፤ደንቦችንና መመሪያዎችን ታሳቢ በማድረግ ባደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ አበረታች ስራዎች መከናወን ችለዋል፡፡ቢሮው በአዋጅ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች መሰረት በማድረግ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወደ ኋላ የሚጎትቱ አመለካከቶችንና አጉል እምነቶችን፣ ልማዳዊ ድርጊቶችንና አሠራሮችን በጠቃሚ የባህል ዕሴቶችለመለወጥ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

Latest News 4 articles

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ ተወሰነ ፤ የውል እድሳት ምዝገባም ከዛሬ ሐምሌ 1 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ ተወሰነ ፤ የውል እድሳት ምዝገባም ከዛሬ ሐምሌ 1 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመግታት ታላቅ እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል።
ከዚህ ቀደም በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት፣ ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ይህንን ተከትሎ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት በይፋ መተግበር ይጀምራል።
ቢሮው እንዳመለከተው ፣ ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ በዘፈቀደ የተወሰነ ሳይሆን በከተማዋ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን እውነተኛ የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ ነው።
ይህ አሰራር በአንድ በኩል አከራዮች ወቅቱንና የኢኮኖሚ ሁኔታውን ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያረጋግጥ ሲሆን ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተከራዮች ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል ከተደጋጋሚ መፈናቀልና ከስነ-ልቦና ስጋት ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያደርጋል።
ውሳኔው በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ረገድ የጎላ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መልካም አስተዳደር ፋይዳዎች እንዳሉት ቢሮው አረጋግጧል።
የአከራይ-ተከራይ ግንኙነትን በሕግ ማዕቀፍ በመምራት የጋራ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን!!
Jul 08, 2026
ሞዴል ብሎኮችን መፍጠር ፅዱ፣ ምቹና ውብ የመኖሪያ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ የአኗኗር ዘይቤን በማዘመን ጤናዉ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር የላቀ አስተዋፅዖ ያለው መሆኑ ተገለጸ።

ሞዴል ብሎኮችን መፍጠር ፅዱ፣ ምቹና ውብ የመኖሪያ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ የአኗኗር ዘይቤን በማዘመን ጤናዉ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር የላቀ አስተዋፅዖ ያለው መሆኑ ተገለጸ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ምርቃትና ከነዋሪዎች ጋር የርክክብ መርሃ ግብር ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል በመሆኑም ህብረተሰቡ አካባቢውን በማስዋብ ለኑሮ ምቹ ውብና ተስማሚ በማድረግ ሞዴል አካባቢን በመፍጠር በመስራት አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወነ ሲሆን ለዚህ ማሳያ በዛሬው ዕለት የተመረቀው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።
የሞዴል ብሎክን መፍጠር ብቻ ሳይሆን ማጠናከርና ማዝለቅ የሚቻለው ሞዴል ቤተሰብ በየብሎኩ መፍጠር ሲቻልና የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን መንከባከብ ብሎም ለፅዳትና ውበት ስራዎች በሀብትና በጉልበት አስተዋፅዖ የሚያበረከቱ ነዋሪዎች ሲበዙ በመሆኑ ሁሉም ነዋሪ የበኩሉን ማበርከት ይገባል ብለዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው የነዋሪውን ሁለንተናዊ ልማትና ብልጽግና የሚያረጋግጡ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ከነዚህም አንዱ ሞዴል አካባቢ ፣ ሞዴል መንደርና ሞዴል ቤተሰብ በመፍጠር ነዋሪዎች ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብታቸው በመሆኑ ሁሉም ለልማቱ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በቀጣይም ማህረሰቡ የሚኖርበትን ብሎክ የተሟላ፣ ለህፃናት ምቹና ዘመናዊ መጫወቻ ያለዉ እንዲሆን በማልማት፣ በማፅዳት፣ በማስዋብ፣ ሠላማዊ ከባቢ በመፍጠር፣ ክ/ከተማዋ ብሎም መዲናችን አዲስ አበባ ለመኖርያ ምቹና ተመራጭ እንድትሆን ቀጣይንነት ባለዉ መልኩ ማልማት ያስፈልጋል ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዱዓለም አሸብር በበኩላቸው በወረዳው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሆን የተቀናጀ ሞዴል መንደር መፍጠር አካባቢውን ውብ ጽዱና ማራኪ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ የሰላም ሰራዊት አባላት ፣የአካባቢው ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
Jul 08, 2026
" በክፍለ ከተማው  በስነ ምግባር የታነጸና በስፖርት የዳበረ ዜጋን ማፍራት የሚያስችሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

" በክፍለ ከተማው በስነ ምግባር የታነጸና በስፖርት የዳበረ ዜጋን ማፍራት የሚያስችሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚገነባ ሁለገብ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
" ፦ አቶ ወልዴ ወገሴ
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚገነባ ሁለገብ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት አስተዳደሩ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ እድገትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስኬታማ ስራዎች ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡
መንግስት የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከሚሰራባቸው ዘርፎች ውስጥ አንዱ ስፖርት መሆኑን በማንሳት በስነ ምግባር የታነፀ፣ ሀገሩን የሚወድና በስፖርት የዳበረ ዜጋ ለእድገትና ለብልፅግና ቁልፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በስነ ምግባር የታነጸና በስፖርት የዳበረ ዜጋ ማፍራት የሚያስችሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡ ለዘርፉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ የሚደነቅ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ስፖርት ለአካልም ሆነ ለአዕምሮ ጤና የማይተካ ሚና እንዳለው በመጥቀስ ማህበራዊ መስተጋብራችንንም የሚያጠነክር በመሆኑ ነዋሪዎች ያላቸውን ሃበትና ጉልበት በማስተባበር ለዘርፉ ያደረጋችሁት ተግባር ለሌሎች አርዓያ የሚሆን ነው ብለዋል።
Jul 08, 2026
“ በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!”

“ በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!”

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አገልግሎት ተጀመረ።


በጉለሌ ክፍለ ከተማ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በ03 የእግር ኳስ ሜዳ ተካሂዷል።
በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ በጎ ፈቃደኝነት ማህበረሰባዊ ትስስርን የሚያጠናክርና የከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
ኃላፊው አክለውም በክረምት ወቅት የሚኖረውን የትራፊክ ፍሰትና ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአደጋ ስጋቶችን ለመቀነስ የወጣቶችና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ቦንኬ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለህዝባችንና ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልጽግና የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልፀው ዛሬ ያስጀመርነው የትራፊክ በጎ ፈቃድ አገልግሎት የዚሁ አንዱ አካል ነው ብለዋል።
የመንገድ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስምሪት የወሰዳችሁ በቅንነትና በታማኝነት ህብረተሰባችሁን በማገልገል መስራት ይጠብቅብናል በማለት ለወጣቶቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱም በትራፊክ ፖሊሶች ለበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስምሪት ተሰጥቷቸዋል።
Jul 08, 2026

Submit Your Complaint or Suggestion

Recent Complaints & Suggestions

Jane Smith

Suggestion: Add more street lights....

2026-07-07 11:48:30
John Doe

The road needs repair....

2026-07-07 11:48:30

Location Map